የልደታ ክ/ከተማ ዳግም ህዳሴ ጤና ጣቢያ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ተሰጥተውታል
- የሀገሪቱን የጤና ፖሊሲና ደረጃ በማገናዘብ የጤና ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስፋፊያ ትምህርት ለነዋሪው አመቺ በሆነ ዘዴ ይሰጣል ወይም እንዲሰጥ ያደርጋል፤
- አጠቃላይ የሆነ የተላላፊ በሽታዎች ቁጥጥርና ቅኝት ያደርጋል፤ ይቆጣጠራል፤ ይከላከላል፤ መረጃዎችን ያሰባስባል፤ ወረርሽኝ ሲነሳ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ይከላከላል፤
- የእናቶችና ህፃናት ጤና ክብካቤ አገልግሎት ይሰጣል ወይም እንዲሰጥ ያደርጋል፤ ይቆጣጠራል፤
- ከፌደራል መንግሥት እና ከዕርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ለተለያዩ ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ የሚሰጡ መድኃኒቶችንና የሕክምና መሳሪያዎችን ያሰራጫል፤ ስራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- የጤና አገልግሎት ፕሮግራሞችን ከሚያካሂዱ መንግሥታዊ ያልሆኑ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር ሕጋዊ ስምምነቶችና ውሎች ይፈጽማል፤ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤
- በተቋሙ ውስጥ የሚከናወኑ የኤች አይ ቪ/ ኤድስና ሌሎች በሽታዎች ቁጥጥር መረጃ ያጠናቅራል፤ በአግባቡ በመተንተን ለሚመለከተው ሪፖርት ያደርጋል፤
- የጤና አጠባበቅ የምክርና የመረጃ አገልግሎት ያደራጃል፤ ይሰጣል፤